የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ32ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ32ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 32ኛ ሳምንት ዛሬ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
የዕለቱ ቀዳሚ መርሐ ግብር መቀሌ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ መድንን ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያገናኛል።
መቀሌ 70 እንደርታ በ30 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ከድል ርቋል።
ኢትዮጵያ መድን በ40 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች አሸንፏል።
ጨዋታው መቀሌ 70 እንደርታ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ፣ ኢትዮጵያ መድን በድል ጉዞው ለመቀጠል የሚያደርጉት ነው።
ድሬዳዋ ከተማ ከባህር ዳር ከተማ ከቀኑ 10 ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።
ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ያላገኘው ድሬዳዋ ከተማ በ34 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።
ባህር ዳር ከተማ በ41 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በ31ኛ ሳምንት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለ ግብ አቻ ተለያይቷል።
ባህር ዳር ከተማ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በርካታ የአቻ ውጤቶችን (17 ጊዜ) ያስመዘገበ ቡድን ነው።
ሁለቱም ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታሉ።
በሌላኛው መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሸገር ከተማ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ38 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ሸገር ከተማ በ40 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በ31ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ መድን የ2 ለ 1 ሽንፈት ሲያስተናግድ ሸገር ከተማ የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ጨዋታው ንግድ ባንክ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ፣ ሸገር ከተማ በድል ጉዞው ለመቀጠል የሚያደርጉት ነው።