አስቶንቪላ ከሊቨርፑል- የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት የሚደረግ ፍልሚያ - ኢዜአ አማርኛ
አስቶንቪላ ከሊቨርፑል- የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት የሚደረግ ፍልሚያ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል።
ምሽት አራት ሰዓት ላይ አስቶንቪላ ከሊቨርፑል በቪላ ፓርክ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ሊቨርፑል እና አስቶንቪላ በተመሳሳይ 59 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው በቅደም ተከተል አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ባለሜዳው አስቶንቪላ ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑልም ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።
የዛሬው ጨዋታ አሸናፊ የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን ያረጋግጣል። ጨዋታው ጠንካራ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።
የ40 ዓመቱ ክሪስ ካቫናግ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት እስከ ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል