ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ ሶስተኛ ቀኑን ባስቆጠረው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተለያዩ ውድድሮች በመካሄድ ላይ ናቸው።

ማምሻውን በተደረገው የ3000 ሜትር መሰናክል የወንዶች የፍጻሜ ውድድር አትሌት ገመቹ ጎዳና 8 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ ከ02 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ ወጥቷል።

አትሌት ገመቹ ለኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ሶስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

በውድድሩ ላይ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሳሙኤል ፍሬው ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል።

በ800 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ አትሌት ምስጋና ኃይሉ እና በ400 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ አትሌት አጃይባ አልዩ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘታቸው ይታወቃል።

ኢትዮጵያ እስከ አሁን በሻምፒዮናው ሶስት የወርቅ፣ አንድ የብር እና ሶስት የነሐስ በድምሩ ሰባት ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

በጋና አክራ እየተካሄደ የሚገኘው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስከ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም