ቀጥታ፡

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች


አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።

በ800 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ አትሌት ምስጋና ኃይሉ 1 ደቂቃ ከ59 ሴኮንድ ከ02 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት አንደኛ ወጥታለች።

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።

ትዕግስት አያና ስድስተኛ እና ሀብታም ገበየሁ ሰባተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

በ400 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ አትሌት አጃይባ አልዩ የመጀመሪያውን ወርቅ ለኢትዮጵያ ማስገኘቷ ይታወቃል።

በ800 ሜትር ፍጻሜ ቦትስዋናዊቷ ኖዌ ኦራቲሌ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ስትጨርስ የኒጀሯ አትሌት ቡባከር ሰሚራ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ እስከ አሁን በሻምፒዮናው ሁለት የወርቅ፣ አንድ የብር እና አንድ የነሐስ በድምሩ አራት ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም