ቀጥታ፡

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ በጋና አክራ እየተካሄደ የሚገኘው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።

በ400 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ውድድር አትሌት አጃይባ አልዩ 51 ሴኮንድ ከ54 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት አንደኛ በመውጣት አሸንፋለች።

ይህም ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ያገኘችው የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳሊያ ሆኖ ተመዝግቧል።

ኢትዮጵያ እምብዛም በማትታወቅበት የአጭር ርቀት ሩጫ ወርቅ ማግኘቷ ተስፋን የፈነጠቀ ሆኖ ተገኝቷል።

ቦትስዋናዊቷ ካምቤሩካ ኦባኬንግ ሁለተኛ እና ጋናዊቷ አጄማንግ ፍሎረንስ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያ እስከ አሁን በሻምፒዮናው አንድ የወርቅ፣ አንድ የብር እና አንድ የነሐስ በድምሩ ሶስት ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስከ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም