በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች በቤተሰብ ደረጃ በምግብ ራስን የመቻል ጥረትን እውን እያደረጉ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች በቤተሰብ ደረጃ በምግብ ራስን የመቻል ጥረትን እውን እያደረጉ ነው
ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፡-በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች በቤተሰብ ደረጃ በምግብ ራስን የመቻል ጥረትን እውን እያደረጉ መሆኑን የሲዳማ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ መምሩ ሞኬ ገለጹ።
"ከተረጂነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በግብርና ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በሐዋሳ ከተማ ተካሄዷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ መምሩ ሞኬ፤ በክልሉ አዳዲስ የግብርና ኢንሼቲቮች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።
በተለይም በሰብል ልማት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በእንስሳት ሀብት ልማት በስፋት ስለመሰራቱ አንስተዋል።
በመሆኑም በክልሉ በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች በቤተሰብ ደረጃ በምግብ ራስን የመቻል ጥረትን እውን እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሸን ኮሚሽነር ወገኔ ብዙነህ፤ እንደ ሀገር የተያዙ በምግብ ራስን የመቻል ግቦችን በመከተል በክልሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ እና ውጤትም እየተገኘባቸው ነው ብለዋል።
በዚህም ከጥቂት ዓመት በፊት እህል ሲሰፈርላቸው የነበሩ በርካታ አርሶ አደሮች ከችግርና ድህነት የወጡ መሆኑን አንስተው በክልሉ የተጀመሩ የግብርና ልማት ኢንሼቲቮች በስፋት የሚቀጥሉ መሆኑን ተናግረዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ለማ መሰለ (ዶ/ር)፤ በበኩላቸው በክልሉ ለአደጋ ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም የመገንባት ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
የክልሉን ልዩ ፀጋና አቅም በመለየት በተሰሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ለሀገር የተረፉ የግብርና ምርቶች እየተመረቱ ይገኛሉ ብለዋል።