ቀጥታ፡

ወላይታ ድቻ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 32ኛ ሳምንት ወላይታ ድቻ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

የቡድኖቹ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሄዷል።

ከተከታታይ ድሎች በኋላ ነጥብ የጣለው ወላይታ ድቻ በ42 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ቅዱስ ጊዮርጊስ በበኩሉ፣ የነጥብ መጠኑን 40 በማድረስ በሰንጠረዡ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም