ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6 /2018 (ኢዜአ):- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካው የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በህንድ ዛሬ በተጀመረው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው።
ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከስብስባው ጎን ለጎን ከደቡብ አፍሪካው የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ሲሆን ሚኒስትሮቹ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።