የኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ ልዩ የአውሮፕላን ትርኢት እያካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ ልዩ የአውሮፕላን ትርኢት እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የማይንቀሳቀስ የአውሮፕላን ትርኢት (Static Airshow) እያካሄደ ይገኛል።
አውሮፕላኖች ለሕዝብ ዕይታ የሚቀርቡበትን ትርኢት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ከፍተውታል።
መርኃ ግብሩ የአየር መንገዱን 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከደንበኞቹና ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ለማክበር ያለመ ነው።
አየር መንገዱ ላለፉት 80 ዓመታት ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመጠቀምና በአፍሪካ ሰማይ ላይ ቀዳሚ በመሆን ሀገራትን በማቀራረብና በዓለም አቀፍ የባህልና የንግድ ልውውጥ ረገድ ወሳኝ ሚና ሲጫወት ቆይቷል