በወራጅ ቀጠና የሚገኘው ምድረ ገነት ሽሬ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
በወራጅ ቀጠና የሚገኘው ምድረ ገነት ሽሬ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ32ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ምድረ ገነት ሽሬ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቤል እንዳለ በ12ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ድሉን ያስመዘገበው ምድረ ገነት ሽሬ በ36 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ላለመውረድ እያደረገ ባለው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
ሆኖም ግን፣ በተመሳሳይ 36 ነጥብ ካለው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር እኩል ቢሆንም፣ በግብ ልዩነት ተበልጦ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በ43 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።
ቡናማዎቹ ባለፉት አራት የሊግ ጨዋታዎች ድል አልቀናቸውም።