ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናገደ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 32ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ደስታ ዋሚሾ በ62ኛው ደቂቃ ግቡን አስቆጥሯል።

በሊጉ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና 55 ነጥብ ላይ ረግቷል።

ባለፉት አራት የሊግ ጨዋታዎች ድል ያልቀናው ሲዳማ ቡና በጥሩ ወቅታዊ ብቃት ላይ አይገኝም።

በውድድር ዓመቱ የተሸነፈባቸው ጨዋታዎች ብዛትም ሰባት ደርሰዋል።

ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ሀዲያ ሆሳዕና በ41 ነጥብ ከነበረበት 15ኛ ደረጃ ወደ 10ኛ ከፍ ብሏል።

በሊጉም 10ኛ ድሉን አስመዝግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም