ቀጥታ፡

የአትሌት የብርጓል መለሰ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈጸመ

 አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፡- የአትሌት የብርጓል መለሰ የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ ተፈጽሟል።
 
የረጅም ርቀት አትሌቷ የብርጓል በመደበኛ የሩጫ ልምምድ ላይ እያለች ከትናንት በስቲያ በድንገት ህይወቷ ማለፉ የሚታወስ ነው።



 
በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ መድረክ ኢትዮጵያን በክብር ያስጠራችው ጀግና አትሌት የብርጓል መለሰ የቀብር ስነ-ስርዓት  በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
 
የቀብር ስነ ስርዓቷም ቤተሰቦቿ ወዳጅ ዘመዶቿ፣ የመከላከያ ሠራዊት አመራር እና አባላት በተገኙበት በመከላከያ የክብር ዘብ እና ማርሽ ባንድ በመታጀብ ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም