ቀጥታ፡

የቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኗ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ወቅታዊና ወሳኝ ሐዋርያዊና ቀኖናዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ በመወያየት ለቤተ-ክርስቲያኗ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ዛሬ ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ጉባኤ ያደርጋል።

የመጀመሪያው ጉባኤ በጥቅምት የሚደረግ ሲሆን፤ ሁለተኛው ርክበ ካህናት ጉባዔ በዓለ ትንሣኤ በዋለ በበዓለ ሃምሳ እኩሌታ በዕለተ ረቡዕ የሚጀመረው ነው።


 

በዚህም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ከሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፤ ዛሬ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ረፋድ ላይ ተጠናቆ መግለጫ ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ጉባኤው በዋነኝነት በሀገር ሰላም በቤተክርስትያን አንድነት ሰለሰው ልጆች ሁሉ ክብርና አንድነት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ሲካሄድ መቆየቱ ገልፀዋል።


 

ጉባዔው ወቅታዊና ወሳኝ ሐዋርያዊና ቀኖናዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ለቤተ-ክርስቲያኗ እና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም