ቀጥታ፡

ኢንተር ሚላን በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ዋንጫውን አነሳ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ በጣልያን የጥሎ ማለፍ ዋንጫ (ኮፓ ኢጣሊያ) የፍጻሜ ጨዋታ ኢንተር ሚላን ላዚዮን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ትናንት ማምሻውን በስታዲዮ ኦሎምፒኮ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ላውታሮ ማርቲኔዝ  እና የላዚዮው ተከላካይ አዳም ማሩሲች በራሱ ላይ  ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢንተር ሚላን ለ10ኛ ጊዜ የጥሎ ማለፉን ዋንጫ አንስቷል። በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ዋንጫውን አስገብቷል።

ኢንተር ባለፈው ሳምንት የሴሪአውን ዋንጫ ለ21ኛ ጊዜ ማንሳቱ የሚታወስ ነው።

የዛሬው የፍጻሜ ተፋላሚ ላዚዮ የጥሎ ማለፉን ዋንጫን ከሰባት ዓመታት በኋላ የማንሳት ህልሙ አልተሳካም።

የሮሙ ክለብ የኮፓ ኢጣሊያን ሰባት ጊዜ አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም