ቀጥታ፡

ፒኤስጂ የፈረንሳይ ሊግ ዋን አሸናፊ መሆኑን አረጋገጠ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ በፈረንሳይ ሊግ ዋን የ29ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር ፒኤስጂ ሌንስን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ትናንት ማምሻውን በቦላሬት- ዴሌሊስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ክቪቻ ክቫራትስኬሊያ እና ኢብራሂም ምባዬ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

በውድድር ዓመቱ  ለ24ኛ ጊዜ ድል የቀናው ፒኤስጂ በ76 ነጥብ አንድ ጨዋታ እየቀረው የሊጉ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።

የሊጉን ዋንጫ ሲያነሳ የአሁኑ ለ14ኛ ጊዜ ነው።

ፒኤስጂ ካለፉት 13 የሊግ ዋንጫዎች 11ዱን በማንሳት ፍጹም የበላይነቱን ይዟል።

በሊጉ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሌንስ በ67 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ሌንስ ዋንጫውን ለማንሳት ያደረገው ብርቱ ፉክክር አድናቆት አስችሮታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም