ቀጥታ፡

የአትሌት የብርጓል መለሰ የቀብር ስነ-ስርዓት ነገ ይፈፀማል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2018 (ኢዜአ)፡- የአትሌት የብርጓል መለሰ የቀብር ስነ-ስርዓት በነገው ዕለት ይፈፀማል።
 
የረጅም ርቀት አትሌቷ የብርጓል በመደበኛ የሩጫ ልምምድ ላይ እያለች በድንገት ህይወቷ ማለፉ ይታወሳል።

በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ መድረክ ኢትዮጵያን በክብር ያስጠራችው ጀግና አትሌት የብርጓል መለሰ የቀብር ስነ-ስርዓት ነገ ከቀኑ ስድስት ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም የኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
 
ፌዴሬሽኑ በአትሌት የብርጓል መለሰ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጆቿ፣ ለአድናቂዎቿ እና ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መፅናናትን ተመኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም