የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከግብጽ ቡድን ጋር አቻ ተለያየ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከግብጽ ቡድን ጋር አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ በ16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እና ግብጽ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
የሁለቱ ቡድኖች የምድብ አንድ ጨዋታ በመሐመድ ስድስተኛ እግር ኳስ ኮምፕሌክስ ተካሄዷል።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው ላይ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ አድርጓል።
በአሜሪካዊው ቤንጃሚን ዚመር የሚሰለጥነው ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ቅዳሜ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከአዘጋጇ ሞሮኮ ጋር ያከናውናል።
በዚሁ ምድብ ዛሬ ምሽት አራት ሰዓት ላይ አዘጋጇ ሞሮኮ ከቱኒዚያ ጋር ትጫወታለች።