ቀጥታ፡

የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሳይንስ ሙዚየምን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሳይንስ ሙዚየም ጉብኝት አድርገዋል።


 

‎የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በሳይንስ ሙዚየም ያደረጉት ጉብኝት፤ ለሁለቱ ሃገራት የመጪው ዘመን የላቀ ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂ እና ከፊት ላሉ ሰፊ ዕድሎች ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ያንጸባረቁበት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ጉብኝቱ ተሻጋሪ ርዕይን የሰነቀ አጋርነት፤ ኢትዮጵያና ፈረንሳይ መጻኢ ጉዟቸው ብሩህ መሆኑን የሚያመለክት መሆኑም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም