ቀጥታ፡

የዓለም አትሌቲክስ ከፍተኛ አመራሮች የአትሌቲክስ ስፖርት መሰረተ ልማቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የዓለም አትሌቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጆን ሪጅን እና የተቋሙ የጨረታዎች፣ ውድድሮች እና ሁነቶች ዳይሬክተር ማርክ ሀርስት የተለያዩ የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶችን ጎበኙ።

በቅርቡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የዓለም አትሌቲክስ የአንድ ቀን ውድድር ያስተናገደውን የአዲስ አበባ ስታዲየም የመሮጫ መም ተመልክተዋል።

በተጨማሪም በመገባደድ ላይ የሚገኘውን አደይ አበባ ዓለም አቀፍ ስታዲየም እና አዲስ ስፖርት ፓርክን ጎብኝተዋል።




አመራሮቹ የተገነቡ የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶች ኢትዮጵያ በቀጣይ ለማዘጋጀት ያቀደቻቸውን ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለማዘጋጀት ጉልህ ሚና እንዳላቸው መግለጻቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።

የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ኢትዮጵያ የ2028 የዓለም አትሌቲክስ "አልቲሜት ሻምፒዮንሽፕ" እና የ2031 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ለማዘጋጀት ባቀረበችው ጥያቄ ዙሪያ ከዓለም አትሌቲክስ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል።

ኢትዮጵያ ውድድሮቹን የማዘጋጀት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት በሚኒስትሯ በኩል ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም