ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከግብጽ አቻው ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2018 (ኢዜአ)፦ 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል።

በውድድሩ 16 ሀገራት ይሳተፋሉ።

ከተሳታፊ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ሞሮኮ፣ ግብጽ እና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላለች።




በአሜሪካዊው ቤንጃሚን ዚመር የሚሰለጥነው ብሔራዊ ቡድኑ ከግብጽ ጋር ከሚደረገው ጨዋታ በፊት የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ቡድኑ በሙሉ ጤንነት እና በጨዋታ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝም አመልክቷል።

የኢትዮጵያ እና ግብጽ ጨዋታ ነገ ከቀኑ 10 ሰዓት በመሐመድ ስድስተኛ እግር ኳስ ኮምፕሌክስ ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም