ቀጥታ፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ሐሙስ ይፈጸማል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ከነገ በስቲያ ይፈጸማል።
 
ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ባደረባቸው ህመም ትላንት ምሽት ህይወታቸው አልፏል።

የኮሚሽነር ዘገየ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ሀሙስ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ስድስት ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም