ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2018(ኢዜአ)፦ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ በመልዕክታቸው፣ አቶ ዘገየ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች የዘመናት ፍትሃዊ ጥያቄ የሆነው መሬት ለአራሹ መልስ እንዲያገኝ በግንባር ቀደምትነት ጉልህ አስተዋጽኦ ያደረጉ ተራማጅ ነበሩ ብለዋል።
ትውልዱ ምንጊዜም ያስታውሳቸዋል ሲሉም ገልጸዋል።