ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ፤ አቶ ዘገየ አስፋው የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች በግፍ የተነጠቁት መሬት እንዲመለስላቸውና የመሬት ሥሪት እንዲቀየር ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱ ናቸው ብለዋል።
በተለያየ ጊዜያት በሚኒስትርነት ሀገራቸውን ማገልገላቸውንም አስታውሰዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በመጨረሻው የእድሜ ዘመናቸው የሀገራችንን ነባር ችግሮች በምክክር ለመፍታት በተቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት እያገለገሉ የነበሩና እጅ አጠሮችን በመደገፍ እድሜያቸውን ሙሉ ሀገራቸውን ያገለገሉ ብርቱ አባት ነበሩ ሲሉም ጠቁመዋል።
የሰላም ዕረፍት እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል።