ቀጥታ፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2018 (ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰጣቸውን ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት እየተወጡ የነበሩ የሀገር ባለውለታ መሆናቸውን የገለጸው ምክር ቤቱ፤ በዚህም ተግባራቸው ታሪክ ሲያስታውሳቸው እንደሚኖር አመልክቷል።

ምክር ቤቱ በኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ሞት የተሰማውን ሀዘን በመግለጽ፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለኮሚሽኑ ማህበረሰብ በሙሉ መፅናናትን ተመኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም