ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ የዋንጫ ፉክክራቸውን አጠናክሩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ የዋንጫ ፉክክራቸውን አጠናክሩ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ረፋድ ላይ ተደርገዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሃዋሳ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
እሙሽ ዳንኤል በ15ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።
ድሉን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ66 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።
በተመሳሳይ ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማህሌት ምትኩ እና በሻዱ ረጋሳ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ66 ነጥብ ተመሳሳይ ነጥብ ባለው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዛል።
ሁለቱ ቡድኖች በመጨረሻው ሳምንት እርስ በእርስ የሚያደርጉት ጨዋታ የዋንጫውን አሸናፊ ይወስናል። ጨዋታው ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል።
በዛሬው ጨዋታዎች ሽንፈት ያስተናገዱት ሃዋሳ ከተማ በ49 ነጥብ አራተኛ እና አዳማ ከተማ በ21 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።