በሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከብሩንዲ ጋር ለሚያደርጋቸው የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።
ግብ ጠባቂዎች መቲ ረታ (ልደታ )፣ ኑዳ ሁሴን (አዲስ ከተማ )፣ ኢትዮጵያ ዴንግ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ) እና ባንቺጊዜ አንተነህ (የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ) ጥሪ ተደርጎላቸዋል።
ማንጠግቦሽ አድማሱ (አርባምንጭ ከተማ )፣ ኤልሻዳይ ዮሴፍ ( ጉለሌ) ፣ ሴና ኤርሚያስ (ለሚኩራ )፣ ቤተልሄም ጌታቸው (ንፋስ ስልክ ላፍቶ)፣ መድሃኒት አለሙ (አርባምንጭ ከተማ)፣ እየሩሳሌም ኤርሚያስ (መቀሌ 70 እንደርታ)፣ መክሊት መሰለ (ጉለሌ ክፍለ ከተማ) እና መሰረት ጌታቸው (ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ) በተከላካይ መስመር የሚገኙ ተጫዋቾች ናቸው።
በአማካይ ክፍል ናጆክ ዱክ ( የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ)፣ ሊያም ዳንኤል (የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ)፣ ጌጤነሽ ተስፋዬ (ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ)፣ ናግዋ ማን (ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ)፣ ለምለም ተስፋዬ (ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ)፣ ኢክራም ሚፍታህ (ደራርቱ ቱሉ አካዳሚ )፣ ትዕግስት ተሾመ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ ቢታኒያ አስተረፍ (ሲዳማ ቡና) ፣ ሊዲያ ሰለሞን (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ) እና ኮከብ ደጀኔ (ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ) በጥሪው ተካትተዋል።
ምህረት ወሰኑ (ሸገር ከተማ)፣ ምህረት አየለ (ቦሌ ክፍለ ከተማ) ፣ ሊዲያ ኢያሱ (ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ) ፣ ሳውያ መሐመድ (ፋሲል ከነማ)፣ እመቤት ዘካሪያስ (ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ)፣ ኦጁሉ ኦዶንግ (ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ)፣ ሲርያ ተሾመ (ጉለሌ ክፍለ ከተማ) እና መታሰቢያ ኃይሉ (አዲስ አበባ ከተማ) በአጥቂ መስመር ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ከዛሬ ጀምሮ ልምምድ ማድረግ እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከብሩንዲ ጋር በያዝነው ግንቦት ወር የማጣሪያ ጨዋታዎቹን ያደርጋል።
ብሔራዊ ቡድኑ በመጀመሪያው ዙር ደቡብ ሱዳንን 8 ለ 0 በሆነ የደርሶ መልስ ውጤት በማሸነፍ ወደ ሁለተኛው ዙር ማለፉ የሚታወስ ነው።
10ኛው የፊፋ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።
በውድድሩ ላይ 24 ሀገራት ይሳተፋሉ። በዓለም ዋንጫው አፍሪካ ሞሮኮን ጨምሮ በአምስት ሀገራት ትወከላለች።
በማጣሪያ የሚያልፉ አራት የአፍሪካ ሀገራት በሶስት ዙሮች በሚደረጉ ጨዋታዎች ይለያሉ።