ቀጥታ፡

24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2018 (ኢዜአ)፦ 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከዛሬ ጀምሮ በጋና አክራ ይካሄዳል።

በጋና ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በሚካሄደው ሻምፒዮና ላይ ከ54 ሀገራት የተወጣጡ አትሌቶች ይሳተፋሉ።

ኢትዮጵያ በውድድሩ 31 ሴቶች እና 32 ወንዶች በድምሩ 63 አትሌቶችን ታሳትፋለች።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ከትናንት በስቲያ አክራ የገባ ሲሆን የመጀመሪያ ልምምዱንም በጋና ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አድርጓል።

ኢትዮጵያ በካሜሮን ዱዋላ በተደረገው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5 ወርቅ፣ 4 ብር እና 1 ነሃስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከአፍሪካ 4ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን፣ ዘንድሮ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል።

በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን የተዘጋጀው ሻምፒዮና እስከ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም