በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቦሌ ክፍለ ከተማ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቦሌ ክፍለ ከተማ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 3/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቦሌ ክፍለ ከተማ ሸገር ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምህረት አየለ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
የግቦቹ ባለቤት ምህረት አየለ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ 12ኛ ድሉን ያስመዘገበው ቦሌ ክፍለ ከተማ በ43 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
ከሁለት ተከታታይ ድሎች በኋላ የተሸነፈው ሸገር ከተማ በ47 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ረግቷል። በውድድር ዓመቱ በአጠቃላይ ስድስተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ የ26ኛ ሳምንት ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ እና መቻል ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።