ቀጥታ፡

ነገሌ አርሲ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 3/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ31ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳዊት መለሰ እና ከቤ ብዙነህ በጨዋታ፣ ዳዊት ተፈራ በፍጹም ቅጣት ምት ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ነገሌ አርሲ በ51 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል። ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ዝቅ አድርጓል።


በውድድር ዓመቱ 13ኛ ድሉንም አስመዝግቧል።

በአንጻሩ በሊጉ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ34 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ዛሬ በተደረገ ሌላኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ 31ኛ ሳምንት ተጠናቋል።

የ32ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም