ቀጥታ፡

የመረጃ ሥርዓትን በማጎልበት ዲጂታል የጤና ስርዓትን ለማጠናከር የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራር ወሳኝ ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 3/2018(ኢዜአ)፦ የመረጃ ሥርዓትን በማጎልበት ዲጂታል የጤና ስርዓትን የበለጠ ለማጠናከር የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚጠናከር የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ።

የጤና ሚኒስቴር ''በዲጂታል ጤና ፈጠራዎች ላይ ዘላቂ ኢንቨስትመንት በማድረግ የጤና ትሩፋቶችን ማሳደግ'' በሚል መሪ ሃሳብ 5ኛው ሀገር አቀፍ የጤና መረጃና ዲጂታል ጤና ሳምንት መርሃ ግብር እያካሄደ ነው


 

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ የጤና ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች፣ የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የሙያና ሲቪል ማኅበራት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚህ ወቅት፤ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራ የጤና ዘርፍ የመረጃ ስርዓትን የሚያዘምን መሰረት ተጥሏል ብለዋል።

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ለጤና ዲጂታል ሥርዓት መጠናከር ትኩረት መሰጠቱንና የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ሥርዓት የጤናውን ዘርፍ በማዘመን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን አስረድተዋል።

ከጤናው ዘርፍ አምስት ምሰሶዎች መካከል የመረጃ ስርዓት አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ጠንካራ የጤና መረጃና ዲጂታል ጤና ለዘርፉ አፈጻጸምና ለሕብረተሰብ ጤና መሻሻል ጉልህ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል።

ሁሉን አቀፍ የጤና ስርዓት ለመዘርጋትና የጤና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ዲጂታል ጤና ወሳኝ ነው ብለዋል።

የዲጂታል ጤና አበረታች ውጤቶችስመዝገቡን ጠቁመው፤ 47 በላይ የዲጂታል ጤና መሳሪያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ሥራ ላይ እየዋሉ ነው ብለዋል።

3ሺህ 500 በላይ የጤና ተቋማት በኸልዝኔት(HealthNet) መገናኘታቸውንና 227 በላይ ተቋማት የታካሚዎችን መረጃ በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት የማካተት ሥራ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማደረጋቸውን አስታውቀዋል

ዩኒቨርሲቲዎች በሰው ሃብት ልማት፣ ምርምርና ፈጠራዎችን በማበረታታት ገንቢ ሚና በመወጣት የመረጃና ዲጂታል ጤና እንዲጠናከር መስራት እንዳለባቸውም ተናግረዋል።


 

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አፀደ ወይን(/) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የጤና መረጃ ስርዓት እንዲዘምን በሰው ኃይል ልማት ላይ በግንባር ቀደምትነት ሲሠራ ቆይቷል ብለዋል።

የጤና መረጃ ስርዓትን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ከጤና ሚኒስቴር እና አጋር አካላት ጋር በመሆን የወረዳዎችን የመረጃ አያያዝ ማዘመን የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።


 

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀማል አባፊጣ(/) ዩኒቨርሲቲው በኦሮሚያ፣ ደቡብ ምዕራብና ጋምቤላ ክልሎች ያሉ ወረዳዎችን የመረጃ አያያዝ ማዘመን የሚያስችል ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመዋል።

በዛሬው እለት ለዩኒቨርሲቲውና የአቅም ግንባታ ድጋፍ ላደረገላቸው ተቋማት የተሰጠው እውቅና ለበለጠ ሥራ የሚያነሳሳ መሆኑን አስረድተዋል።


 

ኢትዮጵያን የአፍሪካ ብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ለተያዘው እቅድ የጤናው ዘርፍ ቁልፍ አስቻይ ተብሎ መለየቱን ያነሱት ደግሞ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዝዳንት ታፈሰ ማቲዎስ(/) ናቸው።

ዘመናዊ መረጃ ስርዓት ጤናማና አምራች ዜጋ ለማፍራት ወሳኝ መሆኑንና የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሚኒስቴር የተጀመረው የጤና መረጃ ስርዓትን የማጠናከር ተግባር እየደገፈ መሆኑን ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ የጤና መረጃ ስርዓትን ዲጂታላይዝ ለማድረግ አስተዋፅኦ ለነበራቸው ስድስት ዩኒቨርሲቲዎችና 11 ወረዳዎች እውቅና ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም