ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ መድን በድል ጉዞው ቀጥሏል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 3/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ31ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳዊት አውላቸው በጨዋታ እና ረመዳን የሱፍ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

የኢትዮጵያ መድኑ አብዱ መሐመድ በራሱ መረብ ላይ ያስቆጠራት ጎል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቸኛ ግብ ሆና ተመዝግባለች።




በሊጉ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ መድን በ40 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም ዘጠነኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ38 ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም