የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን መርሐ ግብር - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን መርሐ ግብር
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 3/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከመቻል ይጫወታሉ።
ድሬዳዋ ከተማ በ24 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። መቻል በ54 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ባለፉት ሶስት የሊግ መርሐ ግብሮች የተሸነፈው ድሬዳዋ ከተማ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።
ተጋጣሚው መቻል ካሸነፈ ተከታታይ አራተኛ የሊግ ድሉን ያስመዘግባል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ቦሌ ክፍለ ከተማ ከሸገር ከተማ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ።
ቦሌ ክፍለ ከተማ በ40 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። ሸገር ከተማ በ47 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በ24ኛ ሳምንት በዋንጫ ተፎካካሪው ኢትዮ ኤሌክትሪክ 1 ለ 0 የተሸነፈው ቦሌ ክፍለ ከተማ ወደ ድል መንገድ ለመመለስ ይፋለማል።
ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ድል የቀናው ሸገር ከተማ በአሸናፊነቱ ለመቀጠል ይጫወታል።