ቀጥታ፡

ይርጋ ጨፌ ቡና እና ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ሁለተኛ መርሐ ግብር ይርጋ ጨፌ ቡና እና ሲዳማ ቡና ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ  ሳቢ እንቅስቃሴ አልተደረገበትም።

የይርጋ ጨፌ ቡናዋ አለሚቱ ብርሃኑ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።

ውጤቱን ተከትሎ ይርጋ ጨፌ ቡና በ18 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።

ሲዳማ ቡና በ35 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም