ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ለ24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ወደ አክራ አቀና

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2018 (ኢዜአ)፦በጋና አክራ ከተማ በሚዘጋጀው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ዛሬ ማለዳ ወደ ስፍራው አምርቷል።

ባለፈው አርብ ሽኝት የተደረገለት ይሄው ልዑክ ቡድን 31 ሴቶች እና 32 ወንዶች በድምሩ 63 አትሌቶችን እንዲሁም 12 አሰልጣኞችን የያዘ ነው።

በተጨማሪም በልዑካን ቡድኑ ውስጥ 3 የህክምና ባለሙያዎች፣ ሶስት የሚዲያ ባለሙያዎች፣ አንድ የቴክኒክ ቡድን መሪ እና የቡድን መሪን ጨምሮ ስድስት ኦፊሻሎች በጉዞው ላይ ተካተዋል።




ኢትዮጵያ በካሜሮን ዱዋላ በተደረገው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5 ወርቅ፣ 4 ብር እና 1 ነሃስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከአፍሪካ 4ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን፣ ዘንድሮ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል።

ይህ ሻምፒዮና ከግንቦት 4 እስከ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም