ሊቨርፑል እና ቼልሲ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ሊቨርፑል እና ቼልሲ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 1/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ36ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሊቨርፑል እና ቼልሲ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራያን ግራቨንበርች በስድስተኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ሊቨርፑል መሪ ሆኗል።
ኤንዞ ፈርናንዴዝ በ35ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል ቼልሲን አቻ አድርጓል።
ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ታይቶበታል።
ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል በ59 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።
ቀያዮቹ የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፏቸውን ማረጋገጥ የሚያስችላቸውን ሶስት ነጥብ ጥለዋል።
ከስድስት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ አንድ ነጥብ ያገኘው ቼልሲ በ49 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቼልሲ እና ድል ከተራራቁ ሰባት ጨዋታዎች አልፈዋል።