ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 1/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ31ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ መቀሌ 70 እንደርታን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፀጋ ከድር በ90ኛው ደቂቃ ግቡን አስቆጥሯል።
ፀጋ ከድር ግቡን ካስቆጠረ በኋላ ማልያውን አውልቆ ደስታውን በመግለጹ ምክንያት በሁለተኛ ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ39 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም 10ኛ ድሉን አሳክቷል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 13ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቀሌ 70 እንደርታ በ30 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ቡድኑ ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።