ቀጥታ፡

በማረቆ ልዩ ወረዳ ከ13 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ

ቆሼ፤ ግንቦት 1/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረቆ ልዩ ወረዳ ከ13 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት በቃ።

ግንባታው የተጠናቀቀውን ፕሮጀክት ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ናቸው።

በምረቃው ላይ እንደተገለጸው የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ከ13 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ከ85 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይም ወጪም ተደርጎበታል።


 

የውሃ ፕሮጀክቱ ከጸሐይ ብርሀን በሚገኝ ሀይል የሚሰራ ፓምፕ የተገጠመለት ሲሆን፣ በልዩ ወረዳው ከንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ጋር በተያያዘ የነበረውን ችግር ያቃልላል ተብሏል። 

በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ  የክልል፣ የልዩ ወረዳው እና የአጎራባች መዋቅር አመራሮችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም