ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 1/2018 (ኢዜአ)፦  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዲሲ ዩናይትድ ጋር የወዳጅነት ጨዋታውን ሐምሌ 4 ቀን 2018  ዓ.ም በዋሺንግተን ዲሲ ያደርጋል።
 
የኢትዮጵያ ሶከር ሌጋሲ (Soccer Legacy) ግጥሚያ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና በዲሲ ዩናይትድ (D.C. United) መካከል የተመሰረተ ዓመታዊ የወዳጅነት ጨዋታ መድረክ  ነው።
 
የሶስተኛ ዓመት ጨዋታው ሐምሌ 4 ቀን 2018  ዓ.ም በዋሺንግተን ዲሲ ኦውዲ ፊልድ ስታዲየም እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
 
በ2017 ዓ.ም በተካሄደ የሶከር ሌጋሲ ጨዋታ ዋልያዎቹ ዲሲ ዩናይትድን 3 ለ 0 ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው።
 
ከሁለት ዓመት በፊት በነበረው የመጀመሪያ መድረክ ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በኦውዲ ፊልድ ስታዲየም መጫወታቸው የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም