ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)) በጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በዓለ ሲመት ላይ ተገኙ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)) በጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በዓለ ሲመት ላይ ተገኙ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 1/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራጩ የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌን የበዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ለመታደም ዛሬ ጅቡቲ ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፤ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ለሃገራቸው የሚሰጡት አገልግሎት የጅቡቲን ሁለንተናዊ እድገት እንዲያስቀጥል ያላቸውን ልባዊ ደስታና መልካም ምኞት ገልጸዋል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለው የቆየ ወዳጅነት እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለሕዝቦቻቸው የጋራ ብልጽግና እንዲሁም ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት መጠናከር መሰረት እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመኝተዋል።