የምስራቋ ፈርጥ ሐረር - ኢዜአ አማርኛ
የምስራቋ ፈርጥ ሐረር
የምስራቋ ፈርጥ ሐረር ከተማ የትላንት ከፍታዋን በሚመጥን ደረጃ በጀጎል ዓለም አቀፍ ቅርስን ጨምሮ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ውጤታማ የኮሪደር ልማት ስራዎች ተከናውነዋል።
የኮሪደር ልማት ስራዎቹም ትላንትን ከዛሬ የሚያስተሳስሩ ነገንም ታሳቢ ያደረጉ ናቸው።
የገናና ስልጣኔ መነሻ ሐረር በየቀኑ ገናናነቷንና እድሜዋን በሚመጥን ደረጃ ከፍታዋን እያረጋገጠች ትገኛለች።
በከተማው የተሰሩና እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለሌሎች የቅርስ ከተሞችም ተሞክሮ በሚሆን ደረጃ የቀደምት አባቶችን አሻራ ሳያደበዝዙ ይልቁንም ተጠብቆ እንዲቆይ በሚያስችልና ተጨማሪ ውበት በሚሆን መልኩ እውን ማድረግ ተችሏል።
በየእለቱ እየፈካች የምትገኘው ሀረር ከተማ ዛሬ ላይ ለመጎብኘት የምታጓጓ ለመኖር የምትመረጥ ለነዋሪዎቿም የተመቸች ከተማ ሆናለች።
ታሪካዊቷ ሀረር ከተማ ዛሬም አዳዲስ ታሪክ እየሰራች ትገኛለች።