ቀጥታ፡

የህዝብን ተጠቃሚነት ለሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶች የተሰጠው ትኩረት ተጠናክሮ ይቀጥላል

ጅማ፤ ሚያዝያ 30/2018 (ኢዜአ)፦ የህዝብን ተጠቃሚነት ለሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶች ግንባታ የተሰጠው ትኩረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ነመራ ቡሊ ገለጹ።

በጅማ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ዛሬ ተመርቀዋል።


 

በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ነመራ ቡሊ፤ በክልሉ ዘላቂ ኢኮኖሚ ለመገንባት ግብ ተጥሎ እየተሰራ ነው።

ለዚህም የህዝብን ተጠቃሚነት ለሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶች ግንባታ ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመው ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።


 

ባለፉት ጥቂት አመታት ሰፊ የስራ ዕድልን በመፍጠር የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት መሆኑን ጠቅሰዋል።

በጅማ ከተማ የተመረቁት ፕሮጀክቶችም የዚሁ አካል ናቸው ብለዋል።

የጅማ ከተማ ከንቲባ ጠሀ ቀመር በበኩላቸው፤ የብልፅግና ጉዟችንን እያረጋገጥን እንቀጥላለን ብለዋል።


 

ከለውጡ በኋላ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች ብዛት ብቻ ሳይሆን ጥራት እና ፍጥነትንም ያማከሉ ናቸው ያሉት አቶ ጠሀ የያዝናቸውን ኢኒሼቲቮች ለማሳካት ሁሌም በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል።

በከተማው በዚህ አመት ከ12 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑን አመልክተዋል።

በከተማው በዛሬው እለት የማምረቻ ሼዶች ፣ የዶሮ እርባታ እና የገበያ ማዕከል እንዲሁም  የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ተመርቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም