ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 30/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የመጀመሪያ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋሉ።

ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ መቻል ከአዲስ አበባ ከተማ ይጫወታሉ።


 

መቻል በ54 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው አዲስ አበባ ከተማ በ12 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ያሸነፈው መቻል በድል ጉዞ ለመቀጠል ወደ ሜዳ ይገባል።

በሊጉ በርካታ ግቦች (50) ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ ከተሸነፈ ወደ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ይወርዳል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ልደታ ክፍለ ከተማ ከባህር ዳር ከተማ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ልደታ ክፍለ ከተማ በ19 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ባህር ዳር ከተማ በተመሳሳይ 19 ነጥብ በግብ ክፍያ በልጦ 10ኛ ደረጃን ይዟል።  

ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ድል ያልቀናው ልደታ ክፍለ ከተማ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይፋለማል።

በ24ኛ ሳምንት በመቻል 3 ለ 2 የተሸነፈው ባህር ዳር ከተማ ወደ ድል መንገድ ለመመለስ ይጫወታል።

ሲዳማ ቡና ከአርባምንጭ ከተማ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

ሲዳማ ቡና በ34 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። ወደ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ መውረዱ የተረጋገጠው አርባምንጭ ከተማ በ10 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።

 

በ24ኛ ሳምንት ልደታ ክፍለ ከተማን 2 ለ 0 ያሸነፈው ሲዳማ ቡና በድል ጉዞው ለመቀጠል ይጫወታል።

ከፕሪሚየር ሊጉ ለወረደው አርባምንጭ ከተማ ጨዋታው ከመርሐ ግብር ማመሟያነት የዘለለ ትርጉም የለውም።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት እስከ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ63 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው። ኢትዮ ኤሌክትሪክ በተመሳሳይ 63 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።


 

የኢትዮ ኤሌክትሪኳ ዳግማዊት ሰሎሞን በ24 ግቦች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራች ይገኛል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ረድኤት አስረሳኸኝ ደግሞ በ20 ግቦች ተከታዩን ስፍራ ይዛለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም