ቀጥታ፡

የመደመር ኢኮኖሚያዊ ዕሳቤዎች እና የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ

የመደመር  መንግሥት ላለፉት ጥቂት ዓመታት ሀገሪቱን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገርመደመርየተሰኘ ሀገር በቀል ፍልስፍናን እንደ መሪ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማዕቀፍ ሲጠቀም ቆይቷል። ይህ ዕሳቤ ብልፅግናን እንደ ዋነኛ ራዕይ በመሰነቅ፣ መደመርን ደግሞ ወደዚያ ግብ ለመድረሻ ስልታዊ መንገድ አድርጎ ይወስደዋል።የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬእንዲሉ የኢትዮጵያ ዘመናዊና ታሪካዊ ስብራቶች ሊጠገኑ የሚችሉት በውጭ ተጽዕኖ ሳይሆን፣ የሀገርን ነባራዊ ሁኔታ፣ ባህላዊ እሴቶች እና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ባገናዘበ የውስጥ አቅም ነው ይህም ኢኮኖሚያዊ መዋቅሩን ከጥገኝነት ወደ ሉዓላዊነት ለመቀየር የሚደረገው ጥረት ዋነኛው ማሳያ ይሆናል

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመደመር ዕሳቤ የተመራው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም እና በመሠረተ ልማት ዘርፎች ጉልህ ለውጦችን አስመዝግቧል። መንግሥት የሽግግር ወቅት ተግዳሮቶችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ መዋቅራዊ ችግሮችን የሚፈቱ የፈጠራ ስልቶችን ተግባራዊ አድርጓል። እነዚህ እርምጃዎች የኢኮኖሚ ዘርፎችን በማስተሳሰር እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ከነገዋ ኢትዮጵያ ራዕይ ጋር በማዋሃድ ረገድ ውጤታማ ሆነዋል። በተለይም በምክንያትና በውጤት ላይ የተመሠረተ አመራርን በመከተል፣ ሀገሪቱ ለዘመናት ከቆየችበት ተረጂነት ወደ ምርታማነት እንድትሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት በስፋት ተከናውነዋል።

በተግባር የታዩ ውጤቶችም የዚህን ዕሳቤ ውጤታማነት የሚያረጋግጡ ናቸው። ኢትዮጵያ ለዘመናት ከኖረችበት የስንዴ ተመጻዋችነት ተላቃ፣ ራሷን ከመመገብ አልፋ ወደ ውጭ መላክ መጀመሯ የታሪካዊ ስኬት ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በነጠላ ዘርፍ ከመመራት ወጥቶ ወደ ብዝኃ የኢኮኖሚ አማራጮች መሸጋገሩን ያሳያል። በተጨማሪም የኢኮኖሚው አቅጣጫ ከፍጆታ ወደ ኢንቨስትመንት በማዘንበሉ፣ የውጭ ዕዳ ጫናን በመቀነስ ወደ ብሔራዊ ምንዳ የሚደረገውን ጉዞ ተጠናክሯል። እነዚህ ለውጦች በዜጎች የኑሮ ደረጃ ላይ ተጨባጭ መሻሻል ለማምጣትና የሀገርን ሉዓላዊነት በኢኮኖሚ ጥንካሬ ለማረጋገጥ ያለሙ ናቸው።

መንግሥት ካከናወናቸው ታላላቅ ፕሮጀክቶች መካከል የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ በመደመር ኢኮኖሚያዊ ዕሳቤ የተገኘ ታሪካዊ ድል ነው። ይህ ፕሮጀክት የሀገራዊ አቅም ማሳያ ብቻ ሳይሆን፣ የቀጣናዊ ትስስር ማጠንጠኛ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል። በተመሳሳይ መልኩ በመዲናችን አዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች የተከናወኑ የከተማ ውበትና የመሠረተ ልማት ሥራዎች፣ የዜጎችን አኗኗር ዘመናዊ ከማድረግ ባለፈ የከተሞችን ጎስቋላ ገጽታ በመቀየር የቱሪዝም መስህብነታቸውን አሳድገዋል። እነዚህ ሥራዎች ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውስብስብ ችግሮችን ተቋቁማ ወደ ተምሳሌታዊ ሀገርነት ለመሸጋገር ያላትን አቅም ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አስመስክረዋል።

ወደፊትም መንግሥት ይህንን አዳጊና ተስፋ ሰጪ የልማት ጉዞ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) የተበሠሩት ሰባቱየጉባ ብሥራቶችከቃል ባለፈ ወደ ተግባር ተሸጋግረው የዜጎችን የኑሮ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀይሩ ይጠበቃል። እነዚህ ስልታዊ ዕቅዶች የኢኮኖሚውን መዋቅር ይበልጥ በማዘመን፣ የሥራ ዕድልን በማስፋፋት እና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍልን በማረጋገጥ ኢትዮጵያን ወደ ሙሉ ብልፅግና ማማ ለማድረስ ያለሙ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም