ባለፉት ስምንት ዓመታት የሚዲያ ምህዳሩን በዲሞክራሲያዊ አውድ ለመዋጀት በወሰድነው እርምጃ ለሀገር ግንባታ የሚረዳ መሠረት ጥሏል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ባለፉት ስምንት ዓመታት የሚዲያ ምህዳሩን በዲሞክራሲያዊ አውድ ለመዋጀት በወሰድነው እርምጃ ለሀገር ግንባታ የሚረዳ መሠረት ጥሏል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2018(ኢዜአ)፦ ባለፉት ስምንት ዓመታት የሚዲያ ምህዳሩን በዲሞክራሲያዊ አውድ ለመዋጀት በወሰድነው እርምጃ ለሀገር ግንባታ የሚረዳ መሠረት ጥሏል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀውና ባለፉት ዓመታት በሚዲያ ዘርፍና ተቋማት ላይ የተመዘገቡ ስኬቶች በቀረቡበት የምክክር መድረክ ላይ ታድሜ ሀሳቤን አጋርቻለሁ ብለዋል።
ይህ ውጤት እንዲቀጥልም ሚዲያዎች ከዋልታ ረገጥነትና ከጽንፈኝነት ወጥተው በእውነት ላይ የተመሠረተ ትርክት በመገንባት፣ ለጋራ ማንነትና ለብሔራዊ መግባባት በቁርጠኝነት ሊሠሩ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።
ሚዲያዎቻችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በጥናት የታገዘ ጥልቅ ትንተና በማቅረብ፣ ከአርዕስት ሽያጭ ባለፈ ለሀገር አጀንዳዎች ትኩረት መስጠት ይኖርባቸዋል ነው ያሉት።
ተግባራቸውም በዓላማ፣ በእይታ፣ በሙያዊ ብቃትና ለህዝብ ቅርብ በመሆን ላይ ተመስርቶ፣ ሚዛናዊነትን በጠበቀ መልኩ ለሀገር ብልጽግና መንገድ ጠራጊና ችግር ፈቺ ሆነው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል በመልዕክታቸው።