ሀላባ ከተማ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
ሀላባ ከተማ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ሀላባ ከተማ ጋሞ ጨንቻን በመለያ ምት አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው የቡድኖቹ ጨዋታ በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት አምርቷል።
በዚህም ሀላባ ከተማ 4 ለ 3 በማሸነፍ የዘንድሮው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አሸናፊ በመሆን በበላይነት አጠናቋል።
ጋሞ ጨንቻ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል።
ሁለቱ ክለቦች በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸው ይታወቃል።
ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ደሴ ከተማ የካ ክፍለ ከተማን 1 ለ 0 በመርታት ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
በዘንድሮው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 21 ክለቦች በሁለት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል።
አቃቂ ክፍለ ከተማ፣ ሐረር ከተማ፣ ነቀምቴ ከተማ፣ ቦዲቲ ከተማ፣ ሶሎዳ አድዋ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ወደ አንደኛ ሊግ የወረዱ ቡድኖች ናቸው።