ለውጡ ትኩረቱን በእሳቤ፣ በህግና አሰራር ላይ በማድረጉ ተቋማዊ ብቃቱ እንዲያድግ አስችሎታል - ኢዜአ አማርኛ
ለውጡ ትኩረቱን በእሳቤ፣ በህግና አሰራር ላይ በማድረጉ ተቋማዊ ብቃቱ እንዲያድግ አስችሎታል
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ ለውጡ ትኩረቱን በእሳቤ፣ በህግና አሰራር ላይ በማድረጉ ተቋማዊ ብቃቱ እንዲያድግ ማስቻሉን የኤንቢሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ ከበደ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት "የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ" በሚል መሪ ሐሳብ ሀገራዊ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
የናሽናል ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ ከበደ ''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በተሰኘው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ በዘርፉ በተለይም በኤንቢሲ ጣቢያ የተመዘገቡትን የለውጡን ስኬቶች አንስተዋል።
ለውጡ ትኩረቱን በዋነኛነት በእሳቤ፣ በህግና አሰራር ላይ በማድረግ፤ ተቋማዊ ብቃትና ሥነ ምግባርን ማጎልበት ማስቻሉን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ለዲጂታላይዜሽን ቅድሚያ በመስጠት፣ የመረጃ ንፉግነትን ባህል በመቀየርና የወል ትርክት በመገንባት ተቀዳሚ የሚዲያ ተቋም መሆን መቻሉን አቶ ብሩክ በመድረኩ ላይ አመልክተዋል።