የኢትዮጵያ የህትመት ዘርፍ የለውጡ መንግሥት ትልቅ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ሪፎርም ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የህትመት ዘርፍ የለውጡ መንግሥት ትልቅ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ሪፎርም ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ ነው
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ የህትመት ዘርፍ የለውጡ መንግሥት ትልቅ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ሪፎርም ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሳፍንት ተፈራ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት "የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ" በሚል መሪ ሐሳብ ሀገራዊ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
በዚሁ ወቅትም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሳፍንት ተፈራ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የህትመት ዘርፍ የለውጡ መንግሥት ትልቅ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ሪፎርም ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ ነው ብለዋል።
በተለይም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያጋጠመውን ተቋማዊ ውስንነቶች በመለየት ተገቢውን ምላሽ መስጠት የሪፎርሙ ተቀዳሚ እርምጃ ነበር ሲሉም አውስተዋል።
የይዘት ጥራትና ብዝኃነትን ማስፋት፣ ሚዲያውን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ ተደራሽነትና ስርጭትን ማሳደግ እንዲሁም ተገቢ አደረጃጀትና መዋቅር መፍጠር የሪፎርሙ ትግበራዎች ዋነኛ ማጠንጠኛዎች እንደነበሩም አስገንዝበዋል።
ይህ የለውጡ መንግሥት ስኬቶች ከዘርፉ ባለፈ የሀገሪቱን የወል ትርክት በመቅረጽ አይነተኛ ሚና መጫወቱንም አቶ መሳፍንት አስረድተዋል።