ደሴ ከተማ በከፍተኛ ሊግ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
ደሴ ከተማ በከፍተኛ ሊግ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የደረጃ ጨዋታ ደሴ ከተማ የካ ክፍለ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አማኑኤል ግዛቸው በ68ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ደሴ ከተማ በከፍተኛ ሊግ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
የካ ክፍለ ከተማ አራተኛ ሆኖ ዓመቱን ጨርሷል።
ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያደጉት ጋሞ ጨንቻ እና ሀላባ ከተማ የከፍተኛ ሊግ ዋንጫን ለማንሳት ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።