ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀረቡበት በጅማ ዞን የጎማ ሁለት ምርጫ ክልል ብልጽግና ፓርቲ እጩዎቹን አስተዋወቀ

ጅማ ፤ ሚያዚያ 28/2018 (ኢዜአ) ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀረቡበት በጅማ ዞን የጎማ ሁለት ምርጫ ክልል ብልጽግና ፓርቲ እጩዎቹን አስተዋውቋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍና አቅም ግንባታ ኃላፊ ነመራ ቡሊ፤ ፓርቲው እስካሁን በርካታ ስኬታማ የልማት ስራዎችን አከናውኖ በቀጣይም ለላቀ ስራ ተዘጋጅቷል ብለዋል።


 

በመደመር እሳቤ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት እየተከናወኑ ላሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የላቀ የመሪነት ሚናቸውን ስለመወጣታቸው አንስተዋል።

በመሆኑም እርሳቸው በሚወዳደሩበት የምርጫ ክልል ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ለምርጫ መዘጋጀታቸው አስደሳች መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይ ፓርቲው የኢትዮጵያን የእድገት ከፍታ እና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማስቀጠል በብቁ እና ጠንካራ ቁመና ላይ የሚገኝ መሆኑንም ተናግረዋል።


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብልጽግና ፓርቲን በመወከል በጎማ ሁለት የምርጫ ክልል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ በመሆን ቀርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም