የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የጀመርነው ጥረት በላቀ ውጤት ቀጥሏል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የጀመርነው ጥረት በላቀ ውጤት ቀጥሏል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የጀመርነው ጥረት በላቀ ውጤት ቀጥሏል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ የሚገኝ የስንዴ ማሳ ዛሬ ተመልክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የጀመርነው ጥረት በላቀ ውጤት ቀጥሏል ብለዋል።
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ በ2,150 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ማሳን ዛሬ ተዘዋውረው መመልከታቸውን ገልጸዋል።